Tuesday, October 12, 2010

Memenan Quen

በስመ እብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እሐዱ እምላክ  እሜን።

በዋሺንግተን ዲሲና እካባቢዋ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት
የምአመናን ቀን አስተባባሪ ኮሚቴ

በዋሺንግተን ዲሲና እካባቢዋ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሥራዓተ አምልኮትን የምንፈጽም  ምዕመናን በየሰንበት ትምህርት ቤቱና በየጉባዓኤው ስለሃይማኖታችንና ስለአገራችን ያገኘነዉን እዉቀትና ፍቅር ይህ ዕድል ላልደረሳቸው የምናካፍልበትና አኛም ስለደረሰን ፀጋ አምላካችንን የምናመሰግንበት ቀን ይኑር በማለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቀን ተመሠረተ።

የዚህ በንቡረእድ ገብረሕይወት መልሴ የበላይ ጠባቂነት ለሁለተኛ ጊዜ የተደራጀው የምዕመናን ስብስባ ዓላማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ሃይማኖትን መሠረታዊ ህግጋት ታሪክ ተውፊትና መንፈሳዊ አገልግሎት አቅም በፈቀደው ማስተዋወቅንና ለቀጣዩ ትውልድ መተላለፍ የሚችልበትን ሁኔታ ማመቻቸትን ያካትታል። ሕዝብ ሳይሰለቸው ይህንን ለመተግበር እንችል ዘንድ መልዕክቶቻችንን ለማስተላለፊያ የመረጥነው የመገናኛ ዘዴ ፡ አዉደ ርእይ፣ ተውኔት ፣ስብከትና መዝሙር የመስሉትን በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ ማቅረብ ነው።

የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥንተ ታሪክ መሠረት ያደረገ ልዩ ዝግጅት ስናቀርብ ፤ የፀጋ ግምጃቤቷን ቃኝተው በኢትዮጲያዊነቶም ኮርተው በረከት ያገኙ ዘንድ የሁለት ቀናት ዝግጅት ተሰናድቷል።

በአሁኑ ወቅት ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙበትን እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ተረድተን እንደየአቅማችን ዕርዳታ መለገስ የምንችልበት ሁኔታም ይጠቆማል። ስለሆነም ማንኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሚያበረክተዉን አሰባስበው ችግሩን በመቅረፍ ረገድ አስተዋጻኦ ማድረግ የሚችሉ ተቋማት ከሕዝብ ጋር እንዲተዋወቁ ይደረጋል።

ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ላይ ወድቀው የጤናና ሌሎችየማሕበራዊ አገልግሎቶችን የሚሹ ወገኖችን ለመርዳት ከሚችሉ ድርጅቶች ጋር እናገናኛለን።

ነፃ የኮምፒውተር ሥልጠና የት እንደሚገኝም መረጃ የሚሰጡ ድርጅቶችን እናቀርባለን።

ከፍ ብለው የተዘረዘሩትን እውን ለማድረግ _______________________ የዝግጅቱ ሙሉ ተካፋይ እንዲሆን እና በሚቻልው ሁሉ እንዲረዳን በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ቅዳሜ መስከረም ፰ ቀን ፪፻፫ ዓ. ም. (September 18, 2010 from 11 am to 7 pm)
ደግሞ ፤ ተንቀሳቃሽ ክሊኒክ በቦታው ተገኝቶ ከጠዋቱ ፭ ሰዓት እስከ ምሽቱ ፩ ሰዓት ደም ግፊት፤ የእርግዝናና፤ የኤች ኣይቪ ቅድም ምርመራ አገልግሎት ይሰጣል።

ቦታው፦       

ዋሽንግተን ሞኑሜንት ሜዳ፤ 15 ኛው መንገድና ኮንስቲትዩሽን አቬኑ
        
Washington Monument grounds, 15th and Constitution Ave, N.W.

ቀንና ሰዓት፦

ቅዳሜ መስከረም ፰ ቀን ፳፻፫ ዓ. ም. ከጠዋቱ ፭ ሰዓት እስከ ምሽቱ ፩ ሰዓት
እሁድ መስከረም ፱ ቀን ፳፻፫ ዓ. ም. ከጠዋቱ ፭ ሰዓት እስከ ምሽቱ ፩ ሰዓት

Saturday, September 18, 2010 11 am thru 7 pm
Sunday, September 19, 2010 11 am thru 7 pm
ወስብሃት ለእግዚአበሔር

የኮሚቴው ሰብሳቢ 

 ዮሐንስ ተክሉ